የእኛ ታሪክ


   እኛ አዳኝ እና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን    ለማምለክ በኮሎምበስ, ኦሃዮ ውስጥ  የሚሰበሰቡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ስደተኞች  እና የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ነን። ግባችን  በመጀመሪያ በኮለምቡስ ቀጥሎም በአሜሪካ  እና በኣለም ዙሪያ ወንገልን መስበክ፣  ደቀመዝሙር ማፍራት እና ክርስቶስን  መምጣት በህብረት መጠባበቅ ነው። በኢየሱስ  ክርስቶስ የሚያምኑ ወንድሞችና እህቶች ፣  እንዲሁም እንግዳ የሆኑ ክርስቶስን  የማያምንቱንም ሁሉ በክርስቶስ ፍቅር  እንቀበላለን።  

የእኛ ተልዕኮ
ማቴዎስ 28: 19-20

እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

እምነታችን

 • በአብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን።
 • እግዚኣብሄር  አምላክ የሰው ልጆችን ፣ የሚታይ እና የማይታየውን ኣለም ሁሉ ፈጣሪ ነው። 
 • እየሱስ ክርስቶስ የእግዚኣብሄር አንድያ ልጅ እንደሆነና ብቸኛ የዓለም ኣዳኝ እንደሆነ እናምናለን።
 • በእያንዳንዱ ክርስቲያን ውስጥ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ  እናምናለን።
 • በ66 መጻህፍት በተሞላው በአምላክ መንፈስ መሪነት በተጻፈው መጽሃፍ ቅዱስ እናምናለን።  ይህም ቅዱስ መጽሃፍ ብጹእ እና ከስህተት የጠራ ቃል ነው፤ የሁሉ ጉዳዮች የመጨረሻው ባለ ሥልጣን ነው። 
 • አምላክ የፈጠረው የሰው ዘር ኃጢአት በመስራቱ ፣ የጠፋ እና ተስፋ የሌለው ሆኖኣል ብለን እናማናለን። ተስፋና መዳን የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል  ብቻ ነው ብለን እናማናለን። 
 • ሞት የእያንዳንዱ ሰው ዘላለማዊ እጣ ነው ብለን እናማናለን። ከእግዚአብሔር የዳኑት  የዘላለም ሕይወት ይወርሳሉ ፤ ከእግዚአብሔር ያልዳኑት፣ የዘላለም ሞትን ይወርሳሉ ብለን እናማናለን።
 • መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና በጸጋ የሚመጣው እንደሆነ እናማናለን። 
 • ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል እና በሁሉም ቦታ ያሉትን ክርስቲያኖች የያዘች ነች ብለን እናማናለን።
 • ጋብቻ ከእግዚአብሔር የተሾመ በአንድ ወንድ እና አንድ ሴት መካከል ያለ ጥምረት ነው ብለን እናምናለን።
 • እኛ በየጊዜው በሚደረግ ጌታ ራት(ኅብረት) ውስጥ በመሳተፍ እናምናለን።

ተከተሉ

ኢየሱስን