የእኛ ተልዕኮ
ማቴዎስ 28: 19-20
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።
እምነታችን
ተከተሉ
- በአብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን።
- እግዚኣብሄር አምላክ የሰው ልጆችን ፣ የሚታይ እና የማይታየውን ኣለም ሁሉ ፈጣሪ ነው።
- እየሱስ ክርስቶስ የእግዚኣብሄር አንድያ ልጅ እንደሆነና ብቸኛ የዓለም ኣዳኝ እንደሆነ እናምናለን።
- በእያንዳንዱ ክርስቲያን ውስጥ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን።
- በ66 መጻህፍት በተሞላው በአምላክ መንፈስ መሪነት በተጻፈው መጽሃፍ ቅዱስ እናምናለን። ይህም ቅዱስ መጽሃፍ ብጹእ እና ከስህተት የጠራ ቃል ነው፤ የሁሉ ጉዳዮች የመጨረሻው ባለ ሥልጣን ነው።
- አምላክ የፈጠረው የሰው ዘር ኃጢአት በመስራቱ ፣ የጠፋ እና ተስፋ የሌለው ሆኖኣል ብለን እናማናለን። ተስፋና መዳን የሚቻለው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ብቻ ነው ብለን እናማናለን።
- ሞት የእያንዳንዱ ሰው ዘላለማዊ እጣ ነው ብለን እናማናለን። ከእግዚአብሔር የዳኑት የዘላለም ሕይወት ይወርሳሉ ፤ ከእግዚአብሔር ያልዳኑት፣ የዘላለም ሞትን ይወርሳሉ ብለን እናማናለን።
- መዳን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና በጸጋ የሚመጣው እንደሆነ እናማናለን።
- ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል እና በሁሉም ቦታ ያሉትን ክርስቲያኖች የያዘች ነች ብለን እናማናለን።
- ጋብቻ ከእግዚአብሔር የተሾመ በአንድ ወንድ እና አንድ ሴት መካከል ያለ ጥምረት ነው ብለን እናምናለን።
- እኛ በየጊዜው በሚደረግ ጌታ ራት(ኅብረት) ውስጥ በመሳተፍ እናምናለን።
ኢየሱስን
ሳምንታዊ አገልግሎቶች
እሁድ አዋቂዎችአገልግሎት
10:30AM-12:30PM
እሁድ ወጣቶችአገልግሎት
9:00AM-10:45PM
ማክሰኞ እና ሐሙስ ጸሎት
6:30 PM- 9PM
ቅዳሜ ጸሎት
10 AM- 1PM